“6ኛዉ ኣገራዊ ምርጫ ዘንድሮ ሊካሄድም ላይካሄድም ይችላል !” – ምርጫ ቦርድ”

ህገወጡ የዱሩዬዎች ስብስብ ብልፅግና ሊቀመንበር ኣብይ ኣህመድ ለህገ ወጡ ስልጣናቸዉ ከፍተኛ ጫና ከደረሰባቸዉ በኋላ በመጪዉ ግንቦት/ሰነ ኣገራዊ ምርጫ ይካሄዳል ሲሉ የሰጡት መግለጫ ኣሁን ባለዉ ኣገራዊ የፀጥታ ችግር ኣገራዊ ምርጫ ላለማካሄድ ተጨማሪ ምክንያት በማቅረብ የሥልጣን ጊዜያቸዉን እንዲራዘም ወስንዋል፡፡
ይህንን ፍላጎታቸዉን ለማሳካትና ህጋዊነትን ለማላበስ ደግሞ በቅርብ ወዳጃቸዉ ወ/ሮ ቡርቱካን ሚዲቅሳ በኩል ኣንድ ማስታወቅያ እንዲለጠፍ ኣርገዋል፡፡ ማስታወቅያዉ ምርጫዉ ለማካሄድ ኣዳጋች ነዉ እምትሉትን በደብዳቤ ኣሳዉቁን ብሏል፡፡ ሙሉ የማስታወቅያዉን ይዘት እንደሚከተለዉ ይቀርባል፡፡
“የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መጪው 6ተኛ አገራዊ ምርጫን አስመልክቶ በሁለት ዙር ከፓርቲዎች ጋር ባካሄደው ምክክር ፓርቲዎች ከመጪው ምርጫ ጋር ተያይዞ አሁን እያጋጠመን ያለ እና ለወደፊትም ያጋጥመናል ያላችኋቸው የፀጥታ፣ የእንቅስቃሴ እና ሌሎች ተያያዥ ችግሮች ማንሳታችሁ ይታወሳል፡፡
በምክክሩ ወቅት በተነገረው መሰረት ፓርቲዎች ለመጪው ምርጫ እንቅስቃሴ ለማድረግ ያጋጥመናል የምትሉትን ችግሮች/ስጋቶች እንዲሁም እስካሁን ያጋጠሙ ችግሮች በዝርዝር በጽሁፍ ከተቻለም ማስረጃዎችን በማያያዝ ለፓለቲካ ፓርቲዎች ክትትል ድጋፍ እና ቁጥጥር ዳይሬክቶሬት እስከ አርብ ጥቅምት 27 ቀን 2013 ዓ.ም ድረስ እንድታስገቡ ጥሪ እናቀርባለን፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ”


0