የፈረንሳይ መንግሥት በቱርክ የሚገኙ ዜጎቹ ለግላዊ ደህንነታቸው ጥንቃቄ እንዲያደርጉ ኣሳሰበ፡፡

የፈረንሳይ መንግሥት ዜጎቹን ያስጠነቀቃቸው በቱርክ በሚገኘው የኤምባሲ ፅህፈት ቤቱ አማካኝነት እንደሆነ ሚድል ኢስት ሞኒተር ፅፏል፡፡
ቀደም ሲል የቱርኩ ፕሬዝዳንት ረሲፕ ጣይብ ኤርዶዋን ሐይማኖታችንን አንቋሻብናለች ያሏትን የፈረንሳይ ምርቶች እና ሸቀጦች ባለ መግዛት እንዲያድሙ ጥሪ አቅርበዋል፡፡
ቱርክ ከዚህም በተጨማሪ በተለያዩ አካባቢየዊ እና በሁለትዮሽ ጉዳዮች ከፈረንሳይ ጋር ውዝግቧ እየተባባሰ ነው፡፡
ውዝግቡ እስከ ጦር ፍጥጫ የዘለቀ ነው ተብሏል፡፡
ሁኔታው በቅርቡ ይሻሻላል ተብሎ እንደማይገመት በመረጃው ተጠቅሷል፡፡
የሁለቱ አገሮች ፕሬዝዳንቶች ብሽሽቅ እየተባባሰ ነው ተብሏል፡፡


0