የዱሩዬዎች ህገወጥ ስብስብ የመከላከል ስራ ባለመስራቱ በኦሮሚያ ክልል፤ ምዕራብ ሀረርጌ ዞን፤ የኣንበጣ መንጋ ሰብሎችን ኣወደመ፡፡

በኦሮሚያ ክልል፤ ምዕራብ ሀረርጌ ዞን፤ በጉባ ቆርቻ ወረዳ በሚገኙ ሁሉም ቀበሌዎች ላይ የተከሰተውን የአንበጣ መንጋ ከባድ ጉዳት ማድረሱንና በመከላከል ረገድ የተደረገ ድጋፍ ስሌለለ መንጋዉን ለመከላከል የአካባቢው መስሪያ ቤቶች ተዘጉ። የአንበጣ መንጋው በወረዳው ከሰፈረ አምስት ቀናት ያስቆጠረ ሲሆን መስሪያ ቤቶቹ ዛሬን ጨምሮ ለአራት ቀናት ስራ ኣቁመዉ ወደ መከላከል ስራ እንዲገቡ ተደርገዋል። የጉባ ቆርቻ ወረዳ የቀድሞዉ አስተዳደር ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ታሪኩ ንጉሴ እንደገለጹት የአንበጣ መንጋው በወረዳው በሚገኙ 24 ቀበሌዎችን ሙሉ ለሙሉ ሸፍኗል። የአንበጣ መንጋው እስከ ትላንት ድረስ ያልነካቸው ሶስት ቀበሌዎችንም ዛሬ ሐሙስ፤ ጥቅምት 5 ማዳረሱንም ተናግረዋል። አካባቢው በማሽላ እና በበቆሎ ምርቶች የታወቀ መሆኑን የሚናገሩት የወረዳው የግብርና ቢሮ ኃላፊ አቶ መሀመድ ሳኒ አሊዬ፤ የአንበጣ ወረርሽኙ በስፋት በታየባቸው ሃያ አንድ ቀበሌዎች ውስጥ ያሉ የአርሶ አደር ማሳዎች በሁለቱ የእህል አይነቶች አዝመራ የተሸፈኑ በአሁኑ ወቅት የአንበጣ መንጋው ሙሉ ለሙሉ ሊባል በሚችል መልኩ በቀበሌዎቹ ያለውን አዝመራ መውረሩንና ማዉደሙን አመልክተዋል።


0
0 0 vote
Article Rating
Subscribe
Notify of
guest
0 Comments
Inline Feedbacks
View all comments