“የኣንበጣዉ መንጋ በሰብል ላይ እያደረሰ ያለዉ ጉዳት ሲታይ ብዙ ክብደት የሚሰጠዉ ኣይደለም፡፡”- የህገ ወጡ የዱሩዬዎች ስብስብ ብልፅግና ሊቀመንበር ኣብይ ኣሕመድ፡፡

በኢትዮጵያ የተከሰተው በረሃ አንበጣ መንጋ ታርሶ በነበረ 420 ሺህ ሄክታር መሬት ላይ ጉዳት ማድረሱን ብዙ የሚጋነንና ክብደት የሚሰጠዉ እንዳልሆነ የህገወጡና የዱሩዬዎች ስብስብ ብልፅግና ሊቀመንበር አብይ አህመድ ገለፁ፡፡ዛሬ የህዝብ ይሁንታዉን ላከተመዉና በህገመንግስቱ የተነፈገዉ ህገወጡ የተወካዮች ምክር ቤት ነኝ ባዩ ስብስብ ኣብይ ኣህመድ ባሰሙት ንግግር እንደገለፁት ከ4 ሚሊየን ከታረሰ መሬት ውስጥ 420 ሺህ ሄክታር መሬት ብቻ ነው በአንበጣ ጉዳት የደረሰበት ጉዳቱ ሀገሪቱ በዘንድሮ አመት ልታመርት ያቀደችውን 35 ሚሊዮን ኩንታል እህልን የሚያሳጣ ስላልሆነ ያን ያህል ክብደት የሚሰጠዉ ኣይደለም ብለዋል፡፡ፍርድ ቤቶች የሚሰጡትን ማንኛውም ውሳኔዎች አስፈፃሚው አካል ኣለማክበሩን የህገወጡና የዱሩዬዎች ስብስብ ብልፅግና ሊቀመንበር አብይ አህመድ በኣለም መገናኛ ብዙሃን ሳይቀሩ መወያያ ርእስ ሁነዉ እየተተቹ ባሉበት በኣሁኑ ወቅት ሁሉንም እንዳለወቁ በመሆን “እኛ ያላከበርነው እና ያልታዘዝነው ፍርድ ቤት ነፃና ገለልተኛ ሆነ ማለት ከንቱ ነው” ሲሉ ኣሹፈዋል፡፡


0
0 0 vote
Article Rating
Subscribe
Notify of
guest
0 Comments
Inline Feedbacks
View all comments