“የኢትዮጵያ ሁኔታ ኣሳስቦናል፡፡”- አውሮፓ ህብረት

የህብረቱ ከፍተኛ ሃላፊ ጆሴፕ ቦሬል ትናንት ባወጡት መግለጫ የኢትዮጵያ ሁኔታ ኣሳስቦናል ሲሉ አስታውቀዋል።
የኢትዮጵያ ጎረቤቶችን ጨምሮ ሁሉም አካላት ውጥረትን ከማባባስ እንዲቆጠቡ፣ ውጥረት አባባሽ ንግግሮችን እንዲያቆሙ እና ከተንኳሽ ወታደራዊ እንቅስቃሴዎች እንዲታቀቡ ያሳሰቡት የህብረቱ ከፍተኛ ሃላፊ ጆሴፕ ቦሬል ፤ ይህን አለማድረግ ሀገሪቱን እና ቀጠናውን አለመረጋጋት ውስጥ ይከታል ሲሉ አስጠንቅቀዋል።
ሁሉንም የፖለቲካ ቡድኖች ያሳተፈ ሀገራዊ ንግግር ከምንጊዜውም በላይ ለኢትዮጵያ አስፈላጊ እንደሆነ የገለፁ ጆሴፕ ቦሬል ለችግሮች ሃይል እና የሃይል ዛቻ መፍትሄ አይሆንም በማለትም አክለዋል።


0