የባንኮች የሚሰበስቡት ተመላሽ የብድር መጠን እየቀነሰ መምጣቱ አሳሳቢ መሆኑ ተገለፀ፡፡

የአገሪቱ ባንኮች እየሰበሰቡ ያሉት የተመላሽ ብድር መጠን እየቀነሰ መምጣቱንና ባንኮቹ በዘንድሮው የመጀመርያ ሩብ ዓመት ያሰባሰቡት ተመላሽ ብድር በ15 በመቶ እንደቀነሰ ተገለጸ፡፡
የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የ2013 ዓ.ም. የመጀመርያ ሩብ ዓመት ይፋዊ መረጃ እንደሚያመለክተው፣ ባንኮች በመጀመርያው ሩብ ዓመት በሦስት ወራት የሰበሰቡት ተመላሽ ብድር 15 በመቶ ቅናሽ ማሳየቱን መጥቀሱ ችግሩን ያሳያል ተብሏል፡፡
ከብድር አመላለስ ጋር ከፍተኛ ቅናሽ የታየባቸው ብድር የወሰዱ ዘርፎች ተብለው ከተለዩት ውስጥ በኢንዱስትሪ፣ በሆቴልና ቱሪዝም፣ ቤቶችና ኮንስትራክሽን ናቸው፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ሰሞናዊ መረጃ እንደሚያመለክተው፣ በተጠናቀቀው ሩብ የበጀት ዓመት የባንኮች ተመለሽ ብድር ከቀዳሚው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ወደ 15 በመቶ ቅናሽ ኣሳይቷል ሲሉ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ገዥ ይናገር ደሴ (ዶ/ር) አመልክተዋል፡፡
በዋናነት ግን ኣሁን በኣገራችን ካለዉ ችግር ኣንፃር በተፈጠረው የኢኮኖሚ መቀዛቀዝ በተለይም ደግሞ በእጅጉ የንግድ እንቅስቃሴያቸው የተጎዳ እንደ ሆቴልና ቱሪዝምና ኮንስትራክሽን የመሳሰሉት የንግድ ዘርፎች ከተፅዕኖው ወጥተው የንግድ እንቅስቃሴያቸው ወደ መስመር እስኪገባ ድረስ ብድር ለመመለስ ጊዜ የሚወስድባቸው ስለሚሆን በባንኮች የተመላሽ ብድር አሰባሰብ ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ እንደሚኖረው ገልጸዋል ሲል ሪፖርተር ጋዜጣ በዛሬዉ እትሙ ለንባብ ኣብቅቷል፡፡


0