“የመከላከያ ሰራዊት ህገመንግስትን የመጠበቅ እንጂ አምባገነናዊ የሆነ ቡድን የመጠበቅ ሃላፊነት የለውም!” ወ/ሮ ፈትለወርቅ ገ/እግዚኣብሄርየህወሓት ምክትል ሊቀመንበር፡፡

“መከላከያ ሃይላችን ሁላችን የምንኮራበት ታሪክ ያለው ለሃገራችን ሰላምና መረጋጋት ማረጋገጥ ብቻ ሳይሆን ከሃገራችን አልፎ ለተለያዩ ሃገሮችም ሰላማቸው እንዲሰፍን ከፍተኛ አስተዋፅኦ ያደረገ ነው። በሃገራችን ህዝቦች ያለው ተቀባይነት ብቻ ሳይሆን ዓለምቀፋዊ ተቀባይነት ያለው ሃይል ነው።አሁን እየሆነ ያለው ግን ህገመንግስታዊ ስርዓቱን ለማዳን ካለው ተልእኮ ውጪ በመሄድ በተለያዩ የህዝብ አመፆችም ይሁን ሰላም የመደፍረስ ሁኔታዎች ባለባቸው እንዲሰማራ እየተደረገ በሌላ መንገድ መፈታት የሚገባው የአከባቢው ህብረተሰብ በመግባባት አካባቢው ላይ ያለ የፖሊስ ሃይል በመጠቀም እንዲሁም የሚነሱ ጥያቄዎች በዲሞክራሲያዊ መንገድ መልስ ከመስጠት ይልቅ መከላከያ ሃይላችን ወደነዚህ አካባቢዎች እንዲሰማራ በማድረግ የመከላከል ስራ እየሰራ አይደለም ያለው። አንደኛ ከህዝቦች ጋር እየተጋጨ ነው ያለው። ሁለተኛ በሁሉም አካባቢዎች ተበትኖ ሃገሪቷ የመጠበቅ ሃላፊነት እየተወጣ አይደለም። ከሁሉም በላይ ደግሞ መከላከያ ሃይላችን ህገመንግስትን የመጠበቅ እንጂ አምባገነናዊ የሆነ ቡድን የመጠበቅ ሃላፊነት አይደለም ያለው። ይህችን ሃገር መታደግ ካለበት ህገመንግስቱን ማእከል በማድረግ መስራት ኣለበት የሚል መልእክት ነው ያለኝ።” ሲሉ መልእክታቸዉን ኣስተላልፈዋል፡፡


0
0 0 vote
Article Rating
Subscribe
Notify of
guest
0 Comments
Inline Feedbacks
View all comments