የሕወሓት ተወካይ በምርጫ ቦርድ መድረክ – ከምርጫ በፊት የፖለቲካ እስረኞች ይፈቱ፡፡ ኣገራዊ መግባባትም መቅደም ኣለበት ሲሉ ኣቋማቸዉ ኣቅርበዋል፡፡

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ምርጫ ቦርድ መጪውን ጠቅላላ ምርጫ በተመለከተ ከፖለቲካ ፓርቲዎች ጋር በሁለት ዙር ከሚያደርገው ውይይት፤ የመጀመሪያውን ጥቅምት 21፤ 2013 በአዲስ አበባው ሃያት ሬጀንሲ ሆቴል አካሂዷል።
በመድረኩ ላይ የተሳተፉ በርከት ያሉ የተቃዋሚ የፖለቲካ ፓርቲ አመራሮች፤ ከምርጫ በፊት የብሔራዊ መግባባት ውይይት መደረግ እንደሚኖርበት በተደጋጋሚ አንስተዋል።
ይህንን ጉዳይ ካስተጋቡት መካከል የህዝባዊ ወያኔ ሓርነት ትግራይ (ሕወሓትን) ወክለው በውይይቱ የተሳተፉት አቶ ዳኘው በለጠ ይገኙበታል።
አቶ ዳኘው ምርጫውን “ሙሽራ የሌለው ሰርግ እንደማካሄድ ነው የምቆጥረው” በማለት ከምርጫው በፊት መቅደም ሰላለባቸው ጉዳዮች ተናግረዋል። “መጀመሪያ ምርጫውን እንዴት ነው መካሄድ ያለበት?” በሚለው ላይ መግባባት ላይ መደረስ አለበት ብለዋል።
የኢትዮጵያ ዜጎች ለማኅበራዊ ፍትህ (ኢዜማ) ፓርቲን የወከሉት ዶ/ር ጫኔ ከበደ፤ የሕወሓቱን ተወካይ ንግግር የስነ ስርዓት ጥያቄ በማንሳት አቋርጠዋል። በምርጫ ቦርድ አመራሮች ፍቃድ በድጋሚ የመናገር ዕድል የተሰጣቸው የሕወሓቱ ተወካይ፤ በግንቦት መጨረሻ አሊያም በሰኔ ይካሄዳል የተባለው መጪው ምርጫ፤ የተሰጠው ጊዜ “የተንዛዛ ነው” ሲሉ ተችተዋል። የኮሮና ወረርሽኝ አነስተኛ በነበረበት ወቅት ተራዝሞ የነበረው ምርጫ፤ አሁን ስፋቱ በጨመረበት ወቅት ለመካሄድ መወሰኑንም ኣሳማኝ ኣይደለም ሲሉ ተወካዩ አንስተዋል።
ዝርዝሩን በቪድዮ እንድትከታተሉት እንጋብዛለን ።


0