የህገወጡ የዱሩዬዎች ስብስብ ብልፅግናና የኦሮምያ ህዝብ የትግል ስልት ዉጥረት ! የኦሮሚያ ልዩ ኃይል መፈረካከስና የኦሮም ነፃነት ጦር ግስጋሴ

በጉልበት ወደ ጦር ውግያ የተላከ ያለው ኦሮሚያ ልዩ ኃይል የሚባለው የብልጥግና ሚልሻ፣ በከፍተኛ ሁኔታ ጉዳት እየደረሰበት ነው።
አብይ አህመድን ሥልጣን ለማቆየት ስባል ብቻ፣ የህዝብን እምብተኝነት በሽብርና በግድያ እንድያፍን ያለ ፍላጎቱ በመታለል፣ የሰለጠነው የብልጥግና ልዩ ኃይል፣የሀገርቷ መከላከያ ሠራዊት ከኦነግ ጦር ግንባር ጋር ለመዋጋት ፍላጎት በማጣቱ ቦታውን ተክተው በግዳጅ ለውግያ እንዲሰማራ ብደረግም፣ ጦርነት በገጠሙት ቦታ ሁሉ ከፍተኛ ጉዳት እየደረሰበት ነው።
አብዛኛው የልዩ ኃይል አባላት ስመለመሉ፣ የኦሮሞን ህዝብ ደህንነትና ድንበሩን ለመጠበቅ አላማ ብቻን አንግተው እንደሚሰለጥኑ ተመልምለው ወደ ስልጠና ብገቡም፣ መጨረሻ ላይ ግን ” ቀና ብለው የሚያህን ሰው እናትህ ብትሆንም ግንባር ግንባሩን ትላለህ!” የሚል ቀጭን ትዕዛዝ ስተላለፍለት ለሌላው አላማ እንደ ተመለመሉ የገባቸውና በተለይም ከአጫሉ ግድያ በኋላ ልዩ ኃይሉ ውስጥ ክፍፍልና የጎረጥ መተያየት በመባባሱ ልዩ ኃይሉ በከፍተኛ ፍጥነት እየፈረሰ ይገኛል። ከዚሁ ጋር ተያይዞ በየቀኑ አፈሙዙን ወደ ግፈኛው ቡድን ለማዞር ጫካ የሚገቡና መሳሪያቸውን በመቶ ሺ ብር መሸጥ እየቻሉ፣ ጫካ ካለው የኦነግ ጦር በነጻ በመሥጠት ወደ ግንባሩ እየተቀላቀሉ ነዉ።
ይህ ልዩ ኃይል በ8 ሬጅመንት የተዋቀረ ስሆን፣ ከ8ቱ የጦር አዛዦች ውስጥ 7ቱ የአንድ መንደር ሰዎችና በድሮው ጊዜ ህዝቡን ስፈጁ የነበሩ የትናንት ቀንደኛ የኦህዴድ አባላት፣ የዛሬ የመሬት፣ ቤት፣ ዶላር፣ ህገ ወጥ የጦር መሳሪያ ዝውውርና የኮንትሮባንድ ንግድ ተዋናይ ግለሰቦች ናቸው።
ይህ ቡድን በብልጥግና ውስጥ ከፍተኛ የሆነ ቀውስ እየፈጠረ ያለና አብይ አህመድን እስከማስፈራራት የደረሰ፣ ሽመልስ አብዲሳን በግድ ሥልጣን ላይ ያቆዬና ከህዝቡ ጋር ደም ካቃባን በኋላ ብቻችን አንጠፋም የሚለው ይህ ቡድን በደምበላሽ ገ/ሚካኤል ይመራል።አባዱላ ገመዳ፣አዳነችና አለሙ ስሜን በሥሩ በመያዝና አብይ አህመድን ተጠቅሞ እንዴት እንደ ሚበላቸው በቅርቡ የሚታይ ይሆናል።
በአንድ ጧት “ሶዳሬ ሥራ መጀመር ይችላል” ተብለው ለኦቦ ድንቁ ዳያሳ ባሌበት በስልክ የተነገረውም ምክንያት ከዚሁ ፍትግያ ጋር እንደሚያያዝ ይገመታል። እምቢ ካልክ ጃዋርና በቀለን ከእስር ቤት በማውጣት በአንድ ሌሊት ወደ ቦታህ እመልሰሃለሁ የሚል ማስፈራሪያም ከዚሁ ጋር ይያዛል።
ወደ ልዩ ኃይሉ ጉዳት ስመለስ ፣ ትናንት ብቻ በጃል ሰኚ የሚመራው በኦሮሚያ ማዕከላዊ ዞን የኦሮሞ ነጻነት ጦር ግንባር ፣ በሰሜን ሸገር ሰላሌ- ከደገም እስከ ኤጀሬ ድረስ ባደረገው ኦፕሬሽን ብያንስ 28 ልዩ ኃይል አባላት ህይወታቸው አልፈዋል! ውጊያው በወራ ጃርሶና ህዳቡ ኣቦተ ወረዳዎች ዛሬም መቀጠሉን ምንጮች ያሳያሉ።
በዚሁ ሁለት ቀናት ውስጥ በጉደር፣ ወሊሶና ጊንጪ አከባቢ በተደረገው የከተማ ውስጥ የማጥቃት ዘመቻም ወደ 7 የብልጥግና አፍቃሪ የህዝብ ጨፍጫፍዎች ተገለዋል፣
በአጠቃላይ በምዕራብ ኦሮሚያ አራቱ የወለጋ ዞኖች የመንግስት መዋቅር ሙሉ በሙሉ ስፈርስ፣ በሰሜንና ምዕራብ ሸገር ገጠራማ አከባቢዎችና የምዕራብ እና ምስራቅ ወለጋ የኢሉባቦርና ቡኖ በደሌ አዋሳኝ ዞኖች በህዝቡ ቁጥጥር ሥር ውለዋል።
አሁን ደግሞ በትግራይ፣ በኤርትራና ብልጥግና መሃከል በተፈጠረው መካረር ምክንያት፣ የልዩ ኃይል አባላት ትግራይን ለመዋጋት ልንቀሳቀሱ ይችላሉ የሚለው ወሬ መናፈስ በመጀመሩ ከፍተኛ መተራመስ እየተፈጠረ ነው። የህዝብን አመጽ በግድያ እንድያፍን ብቻ ተብለው ሰለጠነው ይህ ቡድን የትግራይን መልክአ ምድር እንዴት ተቋቁሞ ሊዋጋ ይችላል የሚል መከራከሪያም እየተነሳ ይገኛል።
በሌላ ዜና ደግሞ ሰሜን ዕዝ ከሰፈረው የሀገር መከላከያ ሠራዊት ጦር አባላት ውስጥ ወደ 24,000 የሚሆኑት የኦሮሞ ልጆች መሆናቸው ስገመት፣ ሰሞኑንን አንዳንዶቹ ከልዩ ኃይሉ አባላት ጋር የስልክ ንግግር እያደረጉ ነው የሚባል ወሬ በመሰራጨቱ፣ በከተሞች መሬትና ቤቶች ንግድ ላይ የተጠመዱት የልዩ ኃይሉ አዛዥ አባላት ውጥረት ውስጥ ገብቷል።
በከተማዎች ላይ ብቻ በጠመንጃ ተንጠልጠለው ያሉት የአብይ አህመድ ጃለዎች በዝርፊያ ላይ ተጠመድዋል፣ የተባበሩት የአረቦች የኢምሬትስ ሪልስተት ነጋዴዎችም ገበያቸው ደርቷል።


0