እንደ ወረደ ! የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ደንበኞች ወደ ሌላ ሰው የባንክ አካውንት ገንዘብ የሚያስገቡበትን አሰራር ከዛሬ ጀምሮ አቋረጠ::

መንግስታዊው የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በተቋሙ የሚገለገሉ ተጠቃሚዎች ወደ ሌላ ሰው የባንክ አካውንት ገንዘብ የሚያስገቡበትን አሰራር አቋረጠ። የባንኩ ደንበኞች እና ተጠቃሚዎች ላይ ይህ ክልከላ የተጣለው ከዛሬ ሰኞ ጥቅምት 09/2013ዓ.ም. ጀምሮ ነው። በአዲስ አበባ በፈረንሳይ ለጋሲዮን አካባቢ በሚገኙ የንግድ ባንክ ቅርንጫፎችን ገንዘብ ወደ ሌላ ሰው የባንክ ሂሳብ ማስገባት እንደማይቻል በባንኩ ሰራተኞች ዛሬ ለደንበኞች መልስ ሲሰጥ ዉሏል። በአካባቢው በሚገኙት በአዋሽ እና በእናት ባንክም ተመሳሳይ ክልከላዎች ተግባራዊ መደረጋቸውን ለማወቅ ተችሏል። በዚያው አካባቢ በሚገኝ የንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የሚሰሩ እና ስማቸው እንዳይገልጽ የጠየቁ የደንበኞች አገልግሎት ኃላፊ፤ ትዕዛዙ ዛሬ ከብሔራዊ ባንክ እንደተላለፈ ገልጸው፤ “ለምን እና በምን ምክንያት እንደተላለፈ ዝርዝር መረጃ አልደረሰንም” ብለዋል። በእናት እና ንብ ባንክ የሚሰሩ የባንክ ባለሙያዎች፤ ተላለፈ የተባለው መመሪያ እስካሁን እንዳልደረሳቸው አስታውቀዋል። የንግድ ባንክ የፈረንሳይ ለጋሲዮን ቅርንጫፍ ደንበኞች አገልግሎት ኃላፊ “ማንኛውም ሰው ገንዘብ ለሌላ የባንክ ሂሳብ መላክ ከፈለገ መጀመሪያ ወደ ራሱ አካውንት በማስገባት ማዘዋወር እንደሚችል” ገልጸዋል። በንብ እና ወጋገን ባንኮች ግን እስከ አምስት ሺህ ብር ድረስ ወደ ሌላ ሰው የባንክ ሂሳብ በጥሬ ገንዘብ ማስገባት እንደሚቻል የየባንኮቹ ሰራተኞች አስረድተዋል። የንብ ባንክ፤ ዮሃንስ ቅርንጫፍ ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ ቢኒያም ተፈሪ “በንግድ ባንክ ከዛሬ ጀምሮ ወደ ሌላ ሰው ገንዘብ ማስገባት እንደማይቻል መረጃ ደርሶኛል” ሲሉ ተናግረዋል። ትዕዛዙ እስካሁን ለንብ ባንክ እንዳልደረሰ የገለጹት ስራ አስኪያጁ፤ “ትዕዛዙ እንደደረሰን ወደዚህኛው አሰራር እንገባለን” ብለዋል። ይህ በሚስጢር የተላለፈ መመርያ ለምን እንደሆነ ግልፅ እንዳልሆነም ለማወቅ ተችሏል፡፡የ104.4 ሬድዮ FM መቐለ መረጃን ለሌሎችም Share በማድረግ ያጋሩ


0
0 0 vote
Article Rating
Subscribe
Notify of
guest
0 Comments
Inline Feedbacks
View all comments