እንደ ወረደ ! ከባእዳዉያን ኣገሮች በኣገርን ጥቅም ከሚደራደርና ኣሳልፎ ከሚሠጥ መሪ ጎን ከመሰለፍ የከፋ የኣገር ክህደት የለም፡፡

ፕረዚዳንት ኢሰያስ ኣፍወርቂ ኢትዮጵያንና ግብፅን ያላቸዉን ችግር እፈተዋለዉ በማለት የጀመሩት ኣንዴ ወደ ግብፅ ኣንዴ ደግሞ ወደ ኣብይ እየተመላለሱ ፖለቲካዊ ይዘት ያላቸዉ ወሬዎች ስያመላልሱ ቆይቷል፡፡
ግብፅ በዙሁ የማግባባት ኣጀንዳ በኩል በኢሰያስ ኣፍወርቅ የኢትዮጵያ ወታደራዊ፣ፖለቲካዊና ተጨባጭ የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ የጀርባ ኣጥንት ናቸዉ የተባሉ ማንኛዉም የኣገሪቷን መሰረተ ልማት የት ቦታ እንደተገነባ ዋና ዋና ፕሮጀክቶች እንዲሰልሉ የቤት ስራ በመስጠት ኣሰማርታቸዉ ቆይታለች፡፡
ኢሰያስ ኣፍወርቂ ካሁን በፊት ኢትዮጵያን ወዳድ በመመሰል ኢትዮጵያን ለማፍረስ ከግማሽ ክፍለዘበን በላይ ሲታገሉ የቆዩ መሆናቸዉ እየታወቀ ሳለ የህገወጡ የዱሩዬዎች ስብስብ ብልፅግና እድር ሊቀመንበር ኣብይ ኣህመድ ሆን ብለዉ የኣገሪትዋን ሉኣላዊነት ኣሳልፈዉ ለመስጠት በመፍቀድ ጭምር ኢሰያስ ማየት ለሚፈልጉት ሁሉ
#-የኢትዮጵያ ኣየር ኃይል
#-የኢትዮጵያ ህዳሴ ግድብን ጨምሮ ግልግል ግቤ ፕሮጀክቶች በሙሉ
#-ሜቴክ
# -የኢትዮጵያ ምድር ሃይል መከላከያ ሰራዊት ተጨባጭ ኣቅም ናቸዉ የተባሉትንና የኣገሪትዋን የድህንነት ቁመና በሙሉ በራቸዉን ከፍተዉ በደንብ እንድያዩትና እንዲሰልሉት መፍቀዳቸዉ ብቻ ሳይሆን በባለሞያዎችም ጭምር ሰፊ ትንተናና ገለፃ እንዲሰጣቸዉ በማዘዝም ጭምር ለስለያ ባለሞያዉ ኢሰያስ ኣፍወርቂ ቆጥረዉ ኣስረክቧል፡፡
ፕረዚዳንት ኢሰያስ ኣፍወርቂ ኣንዴ የኣመሪካ (CIA) ፤ ኣንዴ የኤርትራ ነፃ ኣዉጪ ኣንዴ የግብፅ ፖለቲካዊና ኢኮኖምያዊ ኣማካሪ በመሆን፤ የተለያዩ ኣጎራባች ኣገሮች ተቃዋሚ ወታደራዊ ስልጠና በመስጠትና በማስታጠቅ የተለያዩ የጥፋት ስራዎች ሲሰሩ ቆይተዋል፡፡
ኣሁን ደግም የኢትዮጵያ የትምክህተኞች ጋጋታ ተገን በማድረግ የኢትዮጵያ የትምክህተኞች ባንዴራ ለብሰዉ ጋደም በማለት በኢትዮጵያ ፍቅር መክነፋቸዉ ጭምር በመግለፅ የኢትዮጵያን መፍረስና ዉድመት ህልማቸዉን እዉን ለማድረግ ፖለቲካዊ ትወናቸዉን እየቀጠሉበት ይገኛሉ፡፡
ግብፅ ከፕረዚዳንት ኢሰያስ ኣፍወርቂ ስለ ኢትዮጵያ ምድር ሃይልና ኣየር ኃይል እንዲሁም ሁሉም የኢትዮጵያ የኢኮኖሚ የጀርባ ኣጥንት ናቸዉ የተባሉት የተገነቡትና ገና በግንባታ ላይ ያሉ ፕሮጀክቶች ቆጥራ የስለላ ስራዋን ተረክባለች ብቻ ሳይሆን `ኢትዮጵያ ማናት?` ለሚለዉ ጥያቄ መልስ የሚሰጥ መረጃ ኣሰባስባ ጨርሳለች፡፡
ግብፅ ኢትዮጵያን ዳግም እንዳታንሰራራ ለማድረግና በወታደራዊ ሃይል ኣይቀጡ ቅጣት ለመቅጣት ኣንዴ በደቡብ ሱዳን ወታደራዊ ካምፕ ለመክፈት ካገሪቱ ባለስልጣናት ስተነጋገር እንደነበርና እንደተፈቀደላት በመገናኛ ቡዙሃን ሳይቀር ሲነገር ከቆየ በኋላ ደቡብ ሱዳናዉያን በግልፅ በኣደባባይ ወጥተዉ ‘ ግዛታችን ለፈለግነዉ መንግስት ብናከራየዉና ብንሰጠዉ ኢትዮጵያ ምን ኣገባት?’ እስከ ማለት ደርሰዋል፡፡
ግብፅ በዚሁ ብቻ ኣላቆመችም ኣለም ኣቀፍ እዉቅና ወዳልተሰጣት የሶማል ኣገር ኣካል የሆነችዉን ሶማሊላንድ ድረስ የግብፅ ከፍተኛ ባለስልጣናት ከሶማሊላንድ ባለስልጣናት ጋር በሶማሊላንድ ወታደራዊ ካምፕ ስለምትከፍትበት ሁኔታ ስትመካከርበትና ስታመቻች ቆይታለች፡፡ የህ ስለመሆኑ ኣለም በደንብ ያቀዋል፡፡የብልፅግና እድር ሊቀመንበር ኣብይ ኣህመድም በደምብ ያቃል፡፡
በዉጭ ጉዳይ ሚኒስቴር ቃል ኣቀባይ በኩል በዲና ሙፍቲ በኩል ከኣንዴ ሁለቴ መግለጫ ተሰጥቶበታል፡፡ ይህ ሁሉ ፖለቲካዊ እንቅስቃሴ በኢትዮጵያ ላይ እየተካሄደ ባለበት ጊዜ ታፍራና ተከብራ የኖረች ኣገር ኢትዮጵያ ሉኣላዊነትዋን ኣሳልፎ ለመስጠት ቆርጦ በተነሳዉ ርካሹና ኣቅመ ቢሱ ኣብይ ኣህመድ የኣገሪቱን ክብርና ልኣላዊነት ወደ ገበያ ኣዉርዷል፡፡ ይህ ሁሉ ከተደረገ በኋላ ነገ ‘እኔ በቅንነት ነዉ ያሰብኩት፡፡ እንዲህ ኣልመሰለኝም ነበር!” እሚባል ነገር ኣሰራም፡፡
ግብፅ በኢትዮጵያ ላይ ሰፊ የማጥቃት እርምጃ ለመዉሰድ ብቻ ሳይሆን ኣመሪካ በራስዋ ጊዜ ግድቡን እንድታወድምላት ስትጠይቅና በራስዋ ጊዜ እርምጃ ለመዉሰድ ከኣመሪካ ይሁንታ ለማግኘት በተደጋጋሚ ፕረዚዳንት ዶናልድ ትራምፕን ስታግባባ ቆይታለች፡፡ ዶናልድ ትራምፕ ይሁንታቸዉን ለግብፅ ሰጥቷል፡፡ በዉስጥ ኣዋቂነት የገቡትን ቃል ደግሞ በኣደባባይ ኣጀንዳ እንዲሆን ኣድርገዉታል፡፡
ግብፅ በደቡብ ሱዳንና ሶማሊላንድ ምን እንደሰራች ከኣንድ ፈጣሪ በስተቀር በኣብይና ደመቀ ፊዞ ጭንቅላት እሚታወቅ ነገር የለም፡፡
የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት በተለይ ደግሞ ጀነራል ኣደምና ሙርኮኛዉና ዘላባጁ የተዋፅኦ ጀነራል ብርሃኑ ጁላ ይህን ሁሉ እያወቁ የኣገርን ልኣላዊነት ኣደጋ ላይ ሲወድቅ ዝምታን መምረጣቸዉ ብቻ ሳይሆን ኣብይ ኣህመድ የኣገርን ልኣላዉነት ለባእድ ኣገር ኣሳልፎ ለመስጠት በምያካሂደዉ ያለዉ ሩጫ በማማለያና በርካሽ ጥቅም ተንበርክከዉ የኣገርን ህገመንግስታዊ ተልእኳቸዉን ወደ ጎን በመተዉ ኣገርን ለማንበርከክ በሚካሄደዉ ያለዉ ሩጫ ተባባሪዎች መሆናቸዉን እያረጋገጡ ነዉ፡፡ እነዚህ ሰዎች መቼም ቢሆን በኢትዮጵያ ታሪክ ከተጠያቂነት ኣያመልጡም፡፡
ስለዚህ የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የኣገርን ጥቅም ኣሳልፈዉ ለመስጠት ከቆሙት ጀነራል ኣደም እና ብርሃኑ ጁላ ኣመራር በማፈንገጥ ለናት ኣገሩና ለህገመንግስቱ ዘብ መቆም ኣለበት፡፡ ኣለበለዝያ ግን ባገር መክዳትና ኣገርን በማንበርከክ መጥፎ ታሪክ ከተጠያቂነት እምያመልጥ ኣካል ኣይኖርም፡፡
104.4 ሬድዮ FMመቐለ


0