እንደ ወረደ ! በማደራጀት ስም የኢትዮጵያ መከላከያ ሰራዊት የተጋረጠበት የመፍረስ ስራ ኣሁንም እንደቀጠለ ነዉ፡፡

ሃገሪትዋን በማዳንና ያለማዳን ላይ መስቀለኛ መንገድ የቆመዉ የኢፌዲሪ መከላከያ ሠራዊት በህገወጡ የዱሩዬዎች ስብስብ ብልፅግና የተሰጠዉን ህገወጥ ትእዛዝ ካገሪቷ ህልዉና-ህልዉናቸዉን ባስቀደሙ ጀነራሎች በህገ ወጡ ቡድን የተሰጣቸዉን ትእዛዝ በመቀበል ሁለት ዕዞችን በአዲስ መልክ ለማደራጀት በሚል ምክንያት የማፍረስ ስራ ኣከናወኑ፡፡ ህገወጡ የዱሩዬዎች ስብስብ ሊቀመንበር ኣብይ ኣህመድ በመከላከያ ወታደራዊ መኮነኖች ላይ ያለዉን ጥርጣሬ ከፍታዉን እየጨመረ በመምጣቱ የህገመንግስት ጥያቄዎች በምያነሱና በብልፅግና ጉዞ ደስተኞች ያልሆኑትን በመገለፍ በመደመር ፍልስፍናዉ ለምያምኑ ወደ ኣመራር ላማስወጣት የተዘየደ መላ ለመተግበር እንድያስችለዉ ዘንድ የመከላከያ የማፍረስ ኣሰራር በኣዲስ ኣደረጃጀት ሽፋን ኣሁንም የማፍረስ ስራዉ ተግባራዊ ኣድርግዋል፡፡’የኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የሚሰጡኝን ግዳጆች በፍጥነት ማከናወን ያስችሉኛል ያላቸውን ተጨማሪ ሁለት ዕዞች በአዲስ መልክ ማደራጀቱን አስታወቀ ።’ በሚል ዜና ዛሬ ኣመሻሽ ላይ የህገወጡ የዱርዬዎች ስብስብ መገናኛ ብዙሃን ‘የኢፌዴሪ አገር መከላከያ ሠራዊት የጦር ኃይሎች ጠቅላይ ኤታማዦር ሹም ጄኔራል አደም መሐመድ እና ምክትል ኤታማዦር ሹም ጄኔራል ብርሃኑ ጁላ ጋዜጣዊ መግለጫ ሰጥተዋል’ እያሉ ስያስተጋቡት ብያመሹም እዉነታዉን ግን ኣሁን በስልጣን ላይ ባለዉ እምነት ባጣባቸዉ በተለይ ደግሞ የኦሮሞና የትግራይ ተወላጆች ያነጣጠር የማግለልና የማንሳፈፍ እርምጃ ለመዉሰድ ይህ ኣዲስ ኣደረጃጀት ሁነኛ ምክንያት ኣርጎ እየተጠቀመበት መሆኑን ለማወቅ ተችሏል፡፡ የጦር ኃይል አዛዦቹ በኢፌዴሪ መከላከያ ሠራዊት የለውጥ ስራዎች፣ በሠራዊቱ አደረጃጀትና በወቅታዊ የሠላምና ጸጥታ ሁኔታ ላይ ማብራሪያ ቢሰጥም የቀረበዉ ማብራርያ ግን ጦር ኣዛዦቹን ግራ ኣጋብቷል፡፡”ሠራዊቱ የሚሰጠውን ግዳጅ በፍጥነት ማከናወን እንዲችል ሁለት አዳዲስ ዕዞች ማቋቋም ኣስፈላጊ ሁኖ ተገኝተዋል፡፡” ተብሎ ማብራርያ ቢሰጥም በጦር ኣዛዦቹ ዘንድ “ካሁን በፊት የነበረዉን ድክመት በደንብ ሳይገመገም በቀጥታ ለምን ወደዚሁ ዉሳኔ ለመግባት ኣስፈላጊ ሆነ?” የሚሉ ጥያቄዎች በኣዛዦቹ ቢጭርም ኣዛዦቹ ከመናገር መቆጠብ እንደመረጡ ስማቸዉን ለመግለፅ ያልፈለጉ ለሬድዮ ተቋማችን በሰጡት ቃል ገልፀዋል፡፡ ማዕከላዊና ሰሜን ምዕራብ አዲስ የተደራጁት ዕዞች ሲሆኑ የቀደሙት ምዕራብ፣ ሰሜን፣ ደቡብና ምስራቅ ዕዞች መኖራቸውንም በተሰጠዉ መግለጫ ለማወቅ ተችሏል፡፡


0
0 0 vote
Article Rating
Subscribe
Notify of
guest
0 Comments
Inline Feedbacks
View all comments