ባለ መቶና ሁለት መቶ ኣዲሱን የኢትዮጵያ ብር ኖት ፎርጅድ መሰራቱን ያመነ የኢትዮጵያ ብሄራዊ ባንክ – ህዝቡ ተገቢዉን ጥንቃቄ እንድያደርግ ኣስጠንቅቋል፡፡

ⵥ – ‘ብልፅግና’ የተባለዉ የድሩዬዎች ስብስብ በትግራይ ባለ ሃብቶችና ባለስልጣናት ደብቀዉታል እያለ ዘርን በመለየት ጣቱን ቀስሮ ሲናገርበት የነበረዉ ከፍተኛዉና ከባንክ ኣሰራር ቁጥጥር እይታ ዉጭ ነበር የተባለዉ የብር መጠን ትግራይ ሳይሆን ጁቡቲ ላይ መሆኑንና ፖለቲካዊ ድርድር እየተካሄደ መሆኑን ብሄራዊ ባንኩ ፍንጭ ሰጥቷል፡፡ⵥ – የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ እስካሁን ድረስ በኢኮኖሚ ውስጥ ይዘዋወራል ተብሎ ከሚገመተው 140 ቢሊዮን ብር ዉስጥ ከ90 ቢሊዮን ብር በላይ አዲሱን የብር ኖት ማሠራጨቱን ተናገረ፡፡ⵥ – በኢትዮጵያ እስካሁን ድረስ ኣዲሱን የኢትዮጵያ ብር ኖት ያላየች ባንክ እንዳለች ተገለፀ፡፡ሙሉ ሪፖርቱን ለንባብ ያበቃዉ ሪፖርተር ጋዜጣ በትናንት እትሙ ላይ ነዉ፡፡ ሙሉ ይዘቱ እንደሚከተለዉ ቀርበዋል፡፡ ” የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከ90 ቢሊዮን ብር በላይ አዲሱን የብር ኖት ማሠራጨቱን ተናገረ፡፡ የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ነባሩን በአዲሱ ብር ለመተካት እየተካሄደ ባለው እንቅስቃሴ፣ ከ90.4 ቢሊዮን ብር በላይ አዲሱን ብር ማሠራጨቱንና በአገሪቱ ከሚገኝ አንድ ቅርንጫፍ ውጪ ለ6,561 ቅርንጫፎች መሰራጨቱን አስታውቋል፡፡ ከብር ለውጡ ጋር በተያያዘ ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ጥቅምት 3 በሰጡት መግለጫ እንዳስታወቁት፣ ብሔራዊ ባንክ ከ74.9 ቢሊዮን ብር በላይ አሮጌውን ብር ከተለያዩ የአገሪቱ ክፍሎች ሰብስበዋል፡፡ የባንኩ ምክትል ገዥ አቶ ሰለሞን ደስታ እንደገለጹት፣ በአሁኑ የብር ለውጥ በጥሩ ሁኔታ እየሄደ መሆኑን ጠቁመው፣ ከአንድ ቅርንጫፍ ውጪ በሁሉም የባንክ ቅርንጫፎች አዲሱ የብር ኖት መሠራጨቱን አመልክተዋል፡፡ በአንዱ ቅርንጫፍ አዲሱን የብር ኖት ማድረስ ያልተቻለውም ከፀጥታ ችግር ጋር ስለመሆኑም ሳይጠቅሱ አላለፉም፡፡ በትናንቱ የብሔራዊ ባንክ ከፍተኛ የሥራ ኃላፊዎች ገለጻ፣ ከአዲሱ የብር ኖት ለውጥ ጋር በተያያዘ አዲስ የተከፈቱ የባንክ አካውንቶች ቁጥርን በተመለከተ ከዚህ ቀደም ከተሰጠው መረጃ የተለየ አኃዝ የሌለ መሆኑን ነው፡፡ ከ2 ሳምንት በፊት በዋና ገዥው በተሰጠ መግለጫ በብር ለውጥን ምክንያት ከ580 ሺሕ በላይ አዳዲስ የባንክ ሒሳቦች መከፈታቸው የተገለጸ ቢሆንም፣ ጥቅምት 3 2013 ዓ.ም (ከትናንት በስትያ) መግለጫ የሰጡት ምክትል ገዥው የተከፈቱት አዳዲስ የባንክ ሒሳቦች 273 ሺሕ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ የአካውንቶቹ ቁጥር ከፍና ዝቅ ሊል ይችላል በሚል የጠቀሱት አቶ ሰለሞን፣ በእነዚህ 273 ሺሕ አዳዲስ የባንክ አካውንቶች እስካሁን ከ13.5 ቢሊዮን ብር በላይ መሰብሰቡን ገልጸዋል፡፡ በኢኮኖሚ ውስጥ ይዘዋወራል ተብሎ ከሚገመተው 140 ቢሊዮን ብር አንፃር አሁን የተሠራጨው አዲሱ የብር ኖት የ90 ቢሊዮን ብር አካባቢ በመሆኑ የገንዘብ ለውጡ በጥሩ ሁኔታ እየሄደ መሆኑን የሚያመለክት መሆኑ ተገልጿል፡፡ አሮጌውን የመቶ ብር፣ ከአዲሱ ደግሞ መቶና ሁለት መቶ ብር ኖትን ፎርጅድ ለመሥራት ተሞክሯል፡፡ ነገር ግን ይኼ አዲሱ የብር ኖት በጣም ረቀቅ ያለ የደኅንነት መጠበቂያዎች የተሠራ በመሆኑ፣ ጥረት ሆኖ ይቀራል እንጂ ሊሳካ የማይችል መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ፎርጂድ የብር ኖት ፈፅሞ ከትክክለኛው የብር ኖት የሚለይ፣ እንዲሁም በቀላሉ ማንም ሊለየው የማይችል በመሆኑ አስመስሎ ለመሥራት የማያመች በመሆኑ ኅብረተሰቡ መጠንቀቁ ተገቢ እንደሆነ ገልጸዋል፡፡ይሁንና በእነዚህ በተጠቀሱ አካባቢዎች አስመስለው የሚሠሩ (ሐሰተኛ) ሰዎች በፀጥታ ኃይሎች ይደረስባቸዋል የሚል እምነትን እንዳላቸውም አቶ ሰለሞን አስረድተዋል፡፡ እስከዚያው ድረስ ግን ኅብረተሰቡ በጣም ጥንቃቄ አድርጎ መከታተል አለበት፡፡ አዲሱን ብርና ሐሰተኛውን ብር በቀላሉ መለየት እንደሚቻልም ተናግረዋል፡፡ ‹‹ከዚህም ሌላ ሐሰተኛውን የብር ኖት ዝውውር በመጠኑም ቢሆን ለመቅረፍ፣ ኮማንድ ፖስቱ በየቦታው እየተከታተለ ነው፤›› ያሉት አቶ ሰለሞነ፣ ሌሎች አካላትም ተመሳሳይ መረጃ በመስጠት እየሠሩ ነው፡፡ አዲሱን የብር ኖት ፎርጂድ ለመሥራት አስቸጋሪ ስለመሆኑ የጠቀሱት ኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ የከረንሲ ማኔጅመንት ዳይሬክተር አቶ አበበ ሰንበቱ በበኩላቸው፣ በእያንዳንዱ አዲስ የብር ኖት ከአሥር በላይ የደኅንነት መጠበቂያዎች ያሉና ይህንን በቀላሉ ለመሥራት ስለማይችሉ፣ ሊሠራ ይችል የሚል እምነት እንደሌላቸው ተናግረዋል፡፡ ሆኖም ኅብረተሰቡ እነዚህን ሐሰተኛ ገንዘቦች በቀላሉ ሊለያቸው ስለሚችል ጥንቃቄ ያደርግ ዘንድ አመልክተዋል፡፡ ሐሰተኛ የገንዘብ ሥርጭት አሳሳቢነት ያለመሆኑን የገለጹት ኃላፊዎቹ፣ ቀደም ባለው ጊዜ እንድ ወይም ሁለት ቅጠሎች፣ ሐሰተኛ ገንዘብ የሚሠሩ ቢኖሩም የፀጥታ ኃይሎች ተከታትለው ሊይዟቸው እንደሚችሉ እምነታቸው መሆኑን ተናግረዋል፡፡ ሕገወጥ ወደፊትም ሊኖር ስለሚችል ይህንን ተገንዝቦ ሕዝቡ ለመከላከል እንዳለበትም አስረድተዋል፡፡ በውጭ አለ ከሚባለው የብር ኖት ጋር ተያይዞም በተለይ ጂቡቲ አለ የሚባለውን ብር በተመለከተ ኮማንድ ፖስቱ፣ ጂቡቲ በመሄድ የሠራው ሥራ ስለመኖሩ የጠቀሱት አቶ ሰለሞን፣ ምን ያህል ገንዘብ ሊኖር እንደሚችልና ከፖለቲካ አኳያም ምን መደረግ እንዳለበት እየታየ መሆኑን ገልጸዋል፡፡ ይህም ሆኖ ግን በየቦርደሩ ላይ ቁጥጥር የሚደረግና ገንዘብ እንዳይገባ ቁጥጥር እንደሚደረግ አክለዋል፡፡ በመሆኑ ይህ ገንዘብ የመጨረሻ ዕጣው መምከን ስለመሆኑ ከማብራሪያው ለመረዳት ተችሏል፡፡ ስለዚህ በውጭ የሚገኝ ገንዘብ ሕጋዊ እስካልሆነ ድረስ ይመክናል፡፡ በውጪ የሚገኝ ገንዘብ አዲሱን ገንዘብ እንዲያነቡና ሥራ የጀመሩ የኤትኤም ማሽኖች ቁጥር 5,308 ደርሰዋል፡፡ በቅርቡ 131 የሚሆኑ ማሽኖችም ሥራ ይጀምራሉ ተብሎ ይጠበቃል፡፡ “


0
0 0 vote
Article Rating
Subscribe
Notify of
guest
0 Comments
Inline Feedbacks
View all comments