“በኢትዮጵያ ከባድ ግጭት ሊቀሰቀስ ይችላል!”-ኢነተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ፡፡

ኣሁን የህዝብ ድምፅ ይሁንታ ያላገኘ የብልፅግና ቡድን ከትግራይ ክልል መንግስት ጋር የገባበት ፍጥጫ ከባድ ግጭት ሊቀሰቅስ እና ሀገሪቱን ሊበታትን እንደሚችል ዐለማቀፉ የግጭት አጥኝ ቡድን ኢነተርናሽናል ክራይስስ ግሩፕ ዛሬ ባወጣው አጭር ሪፖርት አስጠንቅቋል፡፡ሁለቱ ለውይይት እንዲቀመጡ ቡድኑ ጥሪ አድርጓል፡፡
የህዝብ ድምፅ ይሁንታ ያላገኘ የብልፅግና ቡድን ያገደውን የትግራይ በጀት ድጎማ እንዲለቅ፣ የትግራይ ክልልም ለውይይት ያስቀመጠውን ቅድመ ሁኔታ እንዲያነሳም አሳስቧል፡፡
አሜሪካ እና አውሮፓ ኅብረት እየተባባሱ በመሄድ ላይ ያሉትን ችግሮች ለማርገብ ግፊት እንዲያደርጉ ቡድኑ በሪፖርቱ ጥሪ አድርጓል፡፡


0