በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በግለሰብ ቤት ውስጥ የተገኘ ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ ኣዲሱን የኢትዮጵያ ብር ኖት በቁጥጥር ስር ዋለ በሚል ሰበብ በህገ ወጡ የብልፅግና ቡዱን እንደተወሰደባቸዉ ተገለፀ።

በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ በግለሰብ ቤት ውስጥ ተገኘ የተባለዉን ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ አዲሱ የብር ኖት በቁጥጥር ስር መዋሉን በመግለፅ ፤ ማንኛዉም ኢትዮጵያዊ ከኣንድ ነጥብ ኣምስት ሚልዮን ብር በላይ መያዝ ክልክል ነዉ በተባለበት ሃገር ኢትዮጵያ ይህ ብር መገኘቱ ከባድ ጥፋት መሆኑን በመግለፅ የግለሰዉ ገንዘብ እንዲወሰድ ተደርገዋል፡፡
ወቅታቂ የገንዘብ ዝውውርን አስመልክቶ ህገወጡ የዱሩዬዎች ስብስብ ብልፅግና ኣብይ ኣህመድ ህገመንግስቱ ማንኛዉም ሰዉ ሃብት የማፍራትና የማካበት እምያዘዉን ኣዋጅ ወደ ጎን በመተዉ ባስተላለፈዉ የባንክ አዋጅ 591/2008 በአንድ ግለሰብ እጅ መገኘት ያለበት የብር መጠን 1.5 ሚሊዮን እና ከዚያ በታች ሲሆን ይህንን ተላልፎ ከተጠቀሰው የብር መጠን በላይ ይዞ የተገኘ ግለሰብ ገንዘቡ እንደሚወረስ በመምርያ በመሻር የሰዉን ገንዘብ ለመዉረስ ትኩረት በመስጠት መስራቱን ሳያሳፍረዉ እንደ ትልቅ ጀብድ በመቁጠር መሸለሉ ኣሳዛኝ መሆኑን የባለ ገንዘቡ ቤተሰብ የሆኑት ገልፀዋል፡፡
ጥቅምት 7 ቀን 2013 ዓ.ም በንፋስ ስልክ ላፍቶ ክፍለ ከተማ ወረዳ 2 ልዩ ቦታው ዶምቦስኮ ት/ቤት አካባቢ በግለሰብ ቤት ውስጥ የተከማቸ ነዉ በሚል ሰበብ 2 ሚሊዮን 222 ሺህ አዲሱ የብር ኖት እንደተወሰደ ለማወቅ ተችሏል፡፡


0