“በብልፅግና የመግለጫ ጋጋታ የዜጎች ድህንነት ኣይረጋገጥም፡፡”-የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የነበሩና ኣሁንም ብስልጣን እንዲቆዩ ከብልፅግና ይሁንታ ያገኙ ኣባላት፡፡

የመግለጫ ጋጋታ ህዝብን ከሞት አያድንምና መንግስት በአማራ ህዝብ ላይ እየተደረገ ያለዉን ጭፍጨፋ ማብራሪያ እንዲሰጥበት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አባላት የነበሩና ኣሁንም ብስልጣን እንዲቆዩ ከብልፅግና ይሁንታ ያገኙ ኣባላት ጠየቁ፡፡
በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ ህይወቱ እያለፈ ያለዉን ህዝብ ድምጽ መወከል አንችልም፡፡ የኢትዮጵያና ህዝቦችዋ ህልዉና ሁሉንም የመጠበቅ ሃላፊነት ያለዉ መንግስት ነዉ ኣሁን በስልጣን ላይ ያለዉ መንግስት ነኝ የሚል ከሆነ ደግሞ ዜጎችን ማዳን ኣለበት ፤ ይህንን ሃላፊነቱን በአግባቡ መወጣት ባለመቻሉ በንጹሃን ዜጎች ላይ ጭፍጨፋ እየደረሰ ነዉ ብለዋል፡፡
በኣማራር በሚገኙ የብልፅግና ኣባላት የሚሰጡት መግለጫ ላይም ብሄሩን ላለመጥቀስ የሚደረግ ማሽሞንሞን ተገቢ ባለመሆኑ የተጨፈጨፈዉ አማራ ነዉ በሚል መስተካከል እንደሚኖርበት የቀድሞዉ የምክር ቤቱ አባላት አንስተዋል፡፡
ሀገሪቱ እንድትፈርስና እንድትበጣበጥ ያደረጉ በጠራራ ፀሓይ ባንክ የዘርፉና ዝም የተባሉትን ሃይሎች ሃይላቸዉን ኣጠናክረዋል ካሉ ብኋላ መንግስት ነኝ እሚለዉ ኣካል የዜጎቹን ደህንነት ለማረጋገጥ ኣቅም ከተሳነዉ ዜጎችን ለእልቂት ባይዳርጋቸዉ ተመራጭ ነዉ ሲሉ ገልፀዋል፡፡
በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ የመከላከያ ሰራዊት በቦታዉ ሲነሳ በምትኩ ሌላ የፀጥታ ሃይል መተካት የነበረበት ቢሆንም ይህ ባለመሆኑ የአሠራር ክፍተት ብቻ ተብሎ መታለፍ የለበትም ሲሉም በተወሰደዉ እርምጃ ወቀሳቸዉን ሰንዝርዋል፡፡


0