በምዕራብ ወለጋ በሰላማዊ ዜጎች ጭካኔ በተሞላበት መንገድ ህይወታቸው እንዳለፈ የኦሮሚያ ክልል መንግስት ነኝ በማለት ለራሱ የሚጠራዉ የዱሩዬዎች ስብስብ ብልፅግና ኣመነ፡፡

የዜጎችን ድህንነት የማስጠበቅ ኣቅም የተሳነዉ የህገወጡ የዱሩዬዎች ስብስብ ብልፅግና በትናትናው እለት በምዕራብ ወለጋ ዞን ጉሊሶ ወረዳ ጋዋ ቀናቲ ቀበሌ ጨለማን ተገን በማድረግ ማንነታቸዉ ባልታወቁ ሃይሎች በተፈፀመው ጥቃት ሰላማዊ ዜጎችን ጭካኔ በተሞላበት መንገድ በአንድ ስፍራ ዉስጥ በርከት ያሉ ዜጎች ህይወታቸው ኣጥተዋል፡፡ የዜጎች በኣሰቃቂ ሁኔታ የተገደሉትን ኣስክሬን እንደተገኙም የኦሮሚያ ክልል መንግስት ነኝ ባዩ ብልፅግና ይፋ ባደረገዉ መግለጫ ኣምንዋል፡፡
ጭካኔ በተሞላበት መንገድ በተፈፀሙ በእነዚህ ተግባራት በህብረተሰቡ ላይ የስነ ልቦና ጫና እንዲፈጠር፣ በስጋት እንዲሞላ እና ከዕለት ተዕለት እንቅስቃሴ ራሱን እንዲገታ በማድረጉ ህዝብ የእለት ተእለት ስራዉን ልያከናዉን ኣልቻለም ያለዉ በመግለጫዉ ፤ በተለይም በምዕራብ ኦሮሚያ አቅጣጫ በሚገኙ ዞኖች ህፃናት፣ ሴቶች፣ አዛውንቶች እና ወጣቶችን ጨምሮ ጭካኔ በተሞላበት በመንገድ እየተገደሉ፣ በእሳት እየተቃጠሉ፣ የአካል ጉዳት እየደርስባቸው እንደሆነና በተቀረዉ ህዝብ ከባድ የስነ ልቦና ጉዳት እንደደርስባቸው ማድረጉ በመግለጫዉ ገልፀዋል፡፡
በኦሮምያ ክልል ኣሁን ከደረሰዉ ከባድና ኣሰቃቂ ጭፍጨፋ ካሁን ቀደምም በተለያዩ ወቅቶች በመንግስት መዋቅር እና በተለያዩ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ የግድያ እርምጃ በመውሰድ ችግሮችን ሲፈጠሩ ቆይተዋል ያለዉ መግለጫው ፤ በተለያዩ ጊዜያትም የፀጥታ እና የአስተዳደር አካላት በተመሳሳይ መንገድ ጫካ ውስጥ በአሰቃቂ ሁኔታ ዜጎች ህይወታቸው ስያጡ ቆይቷል ሲል ገልፅዋል።
በክልሉ በተፈጠረዉ ኣለመረጋጋት በርካታ ቤተሰቦች ተበትነዋል፣ ህፃናትን ያለ አባትና እናት አስቀርቷል ያለው መግለጫው፥ የህዝቡና የግለሰቦች ሀብትም እንዲጠፋ ማድረጉን አስታውሷል።
ትናንት በንፁሃን ዜጎች በተፈፀመው ጥቃት ህይወታቸዉ ላጡ ወገኖች የኦሮምያ የብልፅግና ኣመራር ነኝ ባዩ የተሰማውን ሀዘን በመግለፅ ለቤተሰቦቻቸው መፅናናትን እመኛለሁ ብሏል፡፡
ግድያዉን የፈፀሙት ሃይሎች እስካሁን ድረስ በቁጥጥር ስር ያዋለዉ ተጠርጣሪ እንደሌለ፤ ይህን እኩይ ተግባር ኦነግና ህወሓት ሳይፈፅሙት ኣይቀርም የሚል ግምቱን ቢገልፅም ይህን ሁሉ ጉዳት ሲደርስ የክልሉ መንግስትና የፀጥታ ሃይሎች ለምን የዜጎች ህይወት ኣልታደጉም ለሚለዉ የህዝብ ጥያቄና ብሶት ግን በመግለጫዉ ያሰፈረዉ ነገር የለም፡፡


0