“በህገወጡ የብልፅግና ቡዱን ታጣቂዎች ስለተከበብን የጠራዉ ሰልፍ ሰርዘነዋል፡፡”-ኣብን፡፡

የአማራ ብሔራዊ ንቅናቄ ፓርቲ (አብን) በአማራ ክልል በሚገኙ ከተሞች እና በአዲስ አበባ የጠራውን ሰልፍ መሰረዙን ለቢቢሲ አስታወቀ።
አብን “በአገሪቱ የተለያዩ ክፍሎች በአማራ ሕዝብ ላይ የሚፈጸመውን ዘር ማጥፋት የሚያወግዝ ” የተቃውሞ ሰልፍ ጥቅምት 18 በአማራ ክልል ከተሞች ጥቅምት 22 ደግሞ በአዲስ አበባ ከተማ ሠልፍ ለማካሄድ ጥሪ አስተላልፎ እንደነበረ ይታወሳል።
ዛሬ ጠዋት የፓርቲው ሥራ አስፈጻሚ ኮሚቴ ስለ ሠልፉ ዝርዝር ጉዳዮች ላይ ምክክር እያደረገ ሳለ በፖሊስ መከበቡን እና የፓርቲው አባላት ከቢሯቸው መውጣትም ሆነ መግባት አለመቻላቸውን የፓርቲው ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጣሂር መሐመድ ተናግረዋል።
“እንቅስቃሴያችንን ለመገደብ ሙከራ ተደርጓል። በዚህ ሁኔታ ሠልፉን መምራት ስለማንችል እንዲቀር ተወስኗል” ብለዋል።


0